ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን፡-
- ሎት 1 – የስቴሽነሪ ዕቃዎች
- ሎት 2 – የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 3 – የመኪና ጎማ እና ባትሪ
- ሎት 4 – የደንብ ልብሶች እና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡
፣ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው፡-
- ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱ
- ቲን ነበር ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ07/03/2013 እስከ21/03/2013 ዓ/ም ድረስ የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁTir 13 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 25/ሃያአምስት ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ስዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ጨረታ በየሎቱ በየርዕሱ በእያንዳንዱ ብር 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 በመ/ቤቱ ካርኒ የተቆረጠ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዩ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2 ኮፒ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒዩ ኦርጅናል ሰነዱ ውስጥ በማስገባት በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በ16ኛው ቀን በቀን 22/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁTir 13 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጊዜ 40 የስራ ቀናቶች ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው በቀን 22/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚህ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራችዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁTir 13 ተጫራቾች ቢኖሩም ባይኖሩም ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዕቃ ዓይነት ዝርዝር ከሚገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዕቃ ዝርዝር መረዳት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ቢሮ ቁTir 13 ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በሚሞሉበት ስዓት ስርዝ ድልዝ መኖር የለለበት ሲሆን የዕቃው ናሙና ቢሮ ቁTir 13 በግንባር በመቅረብ ማየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡ የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን በሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በሎት ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሙሉ በሙሉ በሞላ ስለሆነ ከመጫረቻ የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ክፍት ማድረግ የለባችሁም በተጨማሪም የዕቃዎች ብዛት ከበጀት አንፃር ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥራችን 058 117 0033 ወይም 058 117 12 08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ሁሉም ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና በተጠየቀው ሞዴል መሰረት ኦርጅናል መሆን አለባቸ፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያዎች መረጃዎች ካሉ በቢሮአችን በውስጥ ሰሌዳ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፤፤
የደባርቅ ከተማ አስ/ ከተማ ልማት፤ቤቶችና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት