የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የደቡብ ጐንደር ዞን ደ/ታ/ከ/ገንዘብ አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል፡-
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2 – የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 – የደንብ ልብስ
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በየዘርፉ በተጠቀሱት የጨረታ አይነቶች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፣
- የግብር ክፍያ መለያ /ቲን/ቁጥር ያላቸው፣
- ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ /ስፕስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና /ቦንድ/ በሚወዳደሩበት የእቃዎች ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ደብር ታቦር ከተማ አስ/ገን/አካ/ል/ጽ/ቤት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾችየ ጨረታ ሀሣቡን አነድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሰርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ስም ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ ለመግለጽ በደ/ ታ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
- በጋዜጣ የወጣው ጨረታ የሚከፈትበት እለተ በአል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ሰአቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
- ስርዝ ድልዝ ካለ ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ/ተመስርቶ/ መጫረት አይቻልም፣
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንድም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፣
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፣
- አሸናፊው የተመረጠውን አይነት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለበት፣
- የቀረበው ናሙና ግዥ ተፈጽሞ እስኪያልቅ ንብረት ክፍል ይቆያል፣
- ጽ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን አይነት የመግዛት መብት አለው፣
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደ/ታ/ከ/አስ/ገን/ኢ/አካ/ል/ት/ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፣
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱየ ተጠበቀ ነው፣
- ማሳሰቢያ፡- ለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/ኢኮ/አካ/ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስክል ቁጥር 0584412922/0584410348/0584410209 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡
የደቡብ ጐንደር ዞን ደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት