የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2013
የደቡብ ዕዝ 32ኛ ክ/ጦር ግዥ ዴስክ ለመስሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል
- አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች፣
- የታካሚ እና የሲቪል ሠራተኞች አልባሳት ፤
- የፅዳት ዕቃዎች፤
- የስፖርት ቁሳቁሶች ፤
- የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፤
- የዳቦ ማሽን ጀኔሬተር እና ጀኔሬተር መለዋወጫ ዕቃዎች፤
- አላቂ የጋራዥ ዕቃዎች እና የሕንፃ መሣሪያ ዕቃዎች፤
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የኦፊስ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች፤ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት በዘርፉ የተሰማራችሁ ድርጅቶች የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልፅ ሙሉ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተወዳዳሪዎች ይጋብዛል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መምሪያና ፍላጎት የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት አዳማ በሚገኘው የ32ኛ ክ/ጦር ግዥ ቢሮ ቁጥር-04 አዳማ ኃይሌ ሪዞርት 100ሜ ገባ ብሎ ወይም ታንከኛ ካምፕ ግቢ አንደኛ በር ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመግዛት ወደ ተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው ጥቅምት 30/2/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የከፍሉ መዝናኛ ክበብ አዳራሽ ይከፈታል::
NB:- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲሁም ¼ ጨምሮ ወይም ¼ ቀንሶ የመግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0912487407/0908257027 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ32ኛ እ/ክ/ጦር መምሪያ