Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለካሊ ዳጆ ግድብ፣ መስኖና መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውል 5 ትናንሽ ዶዘር እና 15 ገልባጭ ተሽከርካሪዎች ድንጋይ የሚሰሩ ላልተወሰነ ጊዜ በኪራይ ከሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

ሀገር አቀፍ ጨረታ ቁጥር 03/2013

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለካሊ ዳጆ ግድብ፣ መስኖና መሰረተ ልማት ግንባታ ፕሮጀከት ግንባታ አገልግሎት የሚውል 5 ትናንሽ ዶዘር እና 15 ገልባጭ ተሽከርካሪዎች ድንጋይ የሚሰሩ ላልተወሰነ ጊዜ በኪራይ ከሚያቀርቡ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

በዘርፉ ተገቢ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለሚወዳደሩትበት ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ የራሳቸው ካልሆነ ከ3ተኛ ወገን ከውክልና ማስረጃ ተረጋግጦ የተወከለበትን ውክልና አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

* በመሆኑም በጨረታው ስመሣተፍ ያሚችሉ ተጫራቾች፦

 1. በዘርፉ አከራይነት የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው
 2. ቫት የተመዘገቡ
 3. በጨረታ ለመሣተፍ የሚችሉ ከገቢዎችና ጉምሩክ ፍቃድ ያገኘ
 4. የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸው መወዳደር ይችላሉ

* የጨረታ ሰነድ የሚሽጥበት ጊዜና ቦታ፦

 1.  ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 24 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ከደ/ው/ስ/ኮ/ድ ቢሮ ቁጥር 17 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።

* ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ፦

 1.  ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ24ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ ።
 2. በማግስቱ በ25ኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይምወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ::
 3. የጨረታ ዋስትና፡
 4. ማንኛውም ተጫራች ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተቢድ ቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

* የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ ፦

1.የዘመኑ የታደሰ የንግድፈቃድማስረጃ፣ የልዩእሴትታክስተመዝጋቢነትና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 በባንክ የተደገፈ CPO ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው። ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

2. ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0462203944 /0462210021
 • ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 • የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሐዋሳ