የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎመስተዳድር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ /ደሴ ማረሚያ ቤት/ ቀጥሎ ያሉትን እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- የመኪና ጎማዎች፣
- ለደንብ ልብስ የሚሆን ቲትረን
- 6000 የአገርውስጥ ጨርቅ፣ ጥላ፣ ጫማና ሸሚዝ ማቅረብ የሚችሉ ነጋዴዎችን በየስራ ዘርፉ በጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስስዚህ፡
- በየስራ ዘርፋ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ተከታታይ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት የስራ ዘርፍ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ወይም ለመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርበታል።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ በጨረታ ለተሸነፉ ወዲያውኑ ይመለሣል፣
- የጨረታው አሸናፊ በአሸነፈው መሰረት ውል ባይወስድ ያስያዘው ያጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- አንዱ ባቀረበው የጨረታ ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ ማቅረብ የለበትም።
- የጨረታው አሸናፊ ከሆነ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% የሚያስይዝ ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልግ ቢሮ ቁጥር9 በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0331116516 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላል ።
- ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሠነድ ከደሴ ማረ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ክፍሎ መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8:30 ሰዓት ድረስ የጨረታሰነዳቸውን ሞልተው በኤንቨሎፕ ላይ ስማቸውንና ስልክ ቁጥርበመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8:30 ታሽጐ 9፡00 ሰዓትይከፈታል:: ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነበሚቀጥለው የስራ ቀናት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ታሽጐ 9:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- ማረሚያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነበከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ
ቤቶች ኮሚሽን የደቡብ ወሱ መስተዳድር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ