የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ግብዓት ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 09/012
የደቡብ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ ለእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ አገልግሎት የሚውል ሆርሞን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማሰረጃ እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 10000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከባበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከቢሮ የግዥ ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 10መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካሉን ቴክኒካል ሰነድ ፋይናንሻሉን ፋይናንሻል ሰነድ በማለት እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ውስጥ በማድረግ በቢሮ የግዥ ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓትታሽጐ በዕለቱ 10፡05 ሰዓት ተጫራቾች/ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ንብ/ አስ/ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ሳይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ –ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
- በተጨማሪ ተጫራቾች ሲጫረቱ የሚፈለገውን ሆርሞን በስቶክ/ በመጋዘናቸው/ውስጥ ያለ መሆን አለበት፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበሰለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0462121716
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት
የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ቢሮ
ሀዋሳ