የፈሳሽ ናይትሮጂን ማምረቻ ማሽን ጥገናና መለዋወጫ ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 98/12
የደቡብ ክልል እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ለሚዛን፣ ለሀዋሳ፣ ለወላይታ፣ ለወልቂጤ፣ ናይትሮጂን ማምረቻ የተለያዩ የፈሳሽ ናይትሮጂን ማምረቻ ማሽን ጥገናና መለዋወጫ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል።
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳትፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸውን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት 20,000 ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን)፡ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ የቴከኒካልና የፋይናሻል የመጫረቻ ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ በማሸግና ሲፒኦ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ በመከተትና አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 10፡05 ሰዓት ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ–ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:- ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ሕልፍ እንዳሉ ወደ ስላሴ መሄጃ መንገድ ላይ ይገኛል
ለበለጠ መረጃ ፡–በስልክ ቁጥር 046-212-17-16
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ
ሀዋሳ