በድጋሚ የወጣ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያና
የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ አገልግሎት
የሚውል ሆርሞንና ዩኒቨርሳል ሺዝ ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 110/12
የደቡብ ከልል እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ የእንሰሳት ዝርያ ማሻሻያ የሚውል ግብዓት Hormon ፤ universal sheath በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በንግድ ዘርፋ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸዉን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት 20,000 ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር የመድኃኒቶቹን መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና የፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን በተለያዩ ፖሰታ በማሸግና ሲፒኦ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ውስጥ በመክተትና አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾችተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱሥነ–ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ አለፍ እንዳሉ ወደ ስላሴ መሄጃ መንገድ ላይ ይገኛል
ለበለጠ መረጃ :- ስልክ ቁጥር0462121716
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት
የእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ
ሀዋሳ