ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ የሠራተኛ ደንብ ልብስ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የ2012 ዓም የመንግሥት ግብር የከፈሉና ፈቃድ ያሳደሱ፤
- የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin Number/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ ::
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሠነድ እስፔስፊኬሽን ሀዋሳ ከሚገኘው ክልል አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ሳጥን ኦርጅናሉን በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ክልል አርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከወጣ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ሣጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። በ16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል የጨረታ ሰነድን ግዥ ፋ/ን/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የብር 10,000 CPO ማስያዝ አለባቸው።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት
የአርብቶ አደር እና ልዩ ድጋፍ
ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ