ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2012 በጀት ዓመት የገበያ ጥናት መረጃ ሶፍት ዌር ለመተግበር የሚያስችል ቀድሞ የነበረውን ሲስተም መሰረተ ልማት አፕግሬድ ለማድረግ ሰርቨር ተከላ ኮንፊገሬሽን ኢንስታሌሽን ሥራ እና የንግድ ምዝገባና ሌሎች የደንበኞች አገልግሎትን ለመቆጣጠር የሚረዳ የደህንነት ካሜራ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ የስልክ ግንኙነት አገልግሎት በአጠቃላይ የአቅረቦትና ተከላ ሥራ ለማከናወን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ በመሠረት፣
- የ2012 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት የደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ግዥና ፋ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ 1% (አንድ ፐርሰንት) CPO ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማጠቃለል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሠዓት ቢሮው ለዚህ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜና ሰዓት ጨረታ ሂደቱ የሚከናወን ይሆናል::
- ተወዳዳሪዎች ንግድ ፍቃድ ብቃት ማረጋገጫ ልዩ ልዩ ድርጅቱን የሚገልጹ ሕጋዊ ማስረጃዎች በA4 ወረቀት ፊትና ጀርባውን ኮፒ በማድረግ እንዲያቀርቡ አጥብቀን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0462214678 ይጠይቁን፡፡
የደቡብ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ