ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 04/2012
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስ ቢሮ ለ2010 በጀት ዓመት
- ኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር፣ ኤሌክትሮኒክስና ተጓዳኝ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግዥው መጠኑ ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው መ/ቤት ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ ዋስትና ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
- የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 45 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።
- አሽናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 5 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በመያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ዕቃውን አጠናቀው ለማቅረብ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፋይናንስ፣ የቴክኒካል ግምገማና ሲፒኦ ፖስታ ተለይቶ መቅረብ አለበት።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልከ ቀጥር 046-220-39-87 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 046-221-49-02 ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን።
የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት የፋይናንስ ቢሮ