የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
001/2013 ሀ
የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ፤ ጽ/ቤቱ ለሚገለገልባቸው ልዩ ልዩ መኪናዎች አገልግሎት የሚውሉ ጎማዎችን ለመግዛት በሥራው በመስኩ የተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀንና ዓ/ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከጽ/ቤታችን ግዥ ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ገዝቶ መውሰድ የሚቻል መሆኑን እየገለጽን፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው ፤
- በዘመኑ የመንግሥት ግብር የተከፈለበትና ከሚፈለገው የአገልግሎት ግዥ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
- ከሚመለከተው የመንግሥት መ/ቤት የተሰጠ የአቅራቢነትና የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያለው ፤
- ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የጨረታው አሽናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ የሚመለስላቸው መሆኑን፤
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ጎማ በቀጣዮቹ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ወደ ጽ/ቤቱ በመቅረብ ዉል መፈፀም ያለባቸው ሲሆን፤ በተባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተገቢውን ካልፈጸሙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ጽ/ቤቱ የራሱን አማራጭ ለመውስድ የሚገደድ መሆኑን፤
- አሸናፊው ድርጅት ተወዳድሮ ያሸነፈበትን ጎማ እንዲያቀርቡ ውል ከገቡበት ቀንና ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ አጓጉዞ ጽ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ አለበት፤
- ጨረታው ይፋ ከሆነበት ቀንና ዓ/ም ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዶችን ኦሪጅናል ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው ማስገባት ያለባቸው ስለመሆኑና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤታችን ግዥና ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት መሆኑን፣ እንደዚሁም 16ኛዉ ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ጨረታው የሚከፈት መሆኑን ፣
- ጽ/ቤታችን ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን፣
- ጨረታውን አስመልክቶ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ፤
በስልክ ቁጥር፡– 0462204803 ደውሎ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ ርዕሰ
መስተዳድር ጽ/ቤት
ሃዋሳ