ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ደቤወፋ/ግ/ጨ/01-2013
የደቡብ ቤንች ወርዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በወርዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም፡–
- የጽህፈት መሳሪያ፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
- የፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- የእንስሳት መድሃኒት እና
- የባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎችን ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢ ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰርት በጨረታው ላይ ለመወዳደር ለምትፍልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘርው ዝቅተኛ የመ/ቤቱን የመወዳደሪያ መስፈረቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘረፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ላት እና የ2013 በጀት ዓመትን ግብር የከፈሉ/ለች።
- በዘረፉ የአቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ የምትችል እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ላት እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል/የምትችል።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ አሸናፊ ሆነው ሲገኙ የውል ማስከበሪያ የግዥውን ጥቅል ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ፣ ቼክ ወዘተ… ማስያዝ የሚችል/የምትችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ ሲወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ) ለእያንዳንዳቸው የእቃ ዓይነቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨርታው ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 10፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 10፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታውንዶክመንትከደ/ቤ/ወ/ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ እና ንብርት አሰ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ላይ ለእያንዳንዱ የእቃ ዓይነቶች የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዶክመንት መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ፋይናሻሉን 1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ በማድረግ በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተና ያላካተተ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደረጎ ይወሰዳል።
- ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ዶክመንት ሙሉ ከሆነ ተጫራቾቹ ባይገኙም የጨረታ ፖስታቸው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ :- የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ደ/ወርቅ
ስልክ ቁጥር ፡-047 450 80 83/ 047 450 80 27 /047 450 80 03/ 047 450 90 72 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት