የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0049/የአገልግሎት ግዥ/12 ዓ.ም
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የደቡብ ምርጥ ዘር
- ከ2011ዓ/ም-2012ዓ/ም ድረስ ያለ የሁለት አመት የድርጅቱን ሂሳብ በውጭ ኦዲተሮች ለማስመርመር ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ የሂሳብና ኦዲተሮች የምዝገባ ፍቃድ የተሰጣቸው እና ለ2012ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የሙያ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማያያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች አጠቃላይ የስራ ልምዳቸውን በተለይ በማምረቻ ድርጅቶች ውስጥ የሰሩበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለኦዲት ሥራ የሚመደቡ ቋሚ ባለሙያዎች ብዛት ፤የትምህርት ደረጃ ፤ የስራ ልምድ ደረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለ ኦዲት ድርጅቱ አቋም የሚያስረዳ ፕሮፋይል ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ድርጅቱ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የኦዲት ድርጅቱ ከ5ዓመት ያላነሰ የኦዲት አገልግሎት የሰጠ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ሲኖርባቸው ብዙ ልምድ ያላቸው የተሻለ ተመራጭ ይሆናሉ፡፡
- ኦዲት ሥራውን ለመጀመር የሚወስድበትን የሪፖርት ጊዜ በስራ ቀናት በዝርዝር መገለፅ ይኖርበታል፡፡ ስራውን በአጭር ጊዜ የሚጨርሱ የተሻለ ተመራጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ በሁለት ፖስታ ሆኖ የቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ በጨረታው መክፈቻ ቀን የሚከፈት ሆኖ የቴክኒካል አፈፃፀማቸው ከ85% በላይ ያገኙ ተጫራቾች ለስራው ብቁ ናቸው ተብሎ ሲገመት የቴክኒካል አፈፃፀማቸው ከ85% በታች የሆኑ ተጫራቾች ከጨረታው ተሰርዘው የፋይናሻል ፕሮፖዛል እንደታሸገ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸው ከ85% በላይ ያገኙ ተጫራቾች የዋጋማቅረቢያ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል/ ለመክፈት ጥሪ የተደርገላቸው ተጫራቾች በተገኙበት ሀዋሳ ላይ በድርጅቱ ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ሲፒኦ 2% በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቾቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል፡፡
- ማናቸውም የመንግስት ታክስና ግብር ወጪ የሚሸፈነው በአገልግሎት ሰጪው በተጫራቹ ድርጅት ይሆናል፡፡
- የሂሳብ ምርመራው የሚካሄደው በድርጅቱ ጽ/ቤት ሀዋሳ ላይ ነው፡፡
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ ግዥና/ፋ/ ንብ/አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ/ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት ሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አካባቢ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጉ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት አስቀድመው ሀዋሳ በድርጅቱ ጽ /ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለፀ በ5 ቀናት ጊዜ ውስጥ ቀርበው ውል መፈራረም አለበት፡፡ ካልፈረሙ ለጨረታው ያስያዙት 2% ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ድርጅቱየተሻለመንገድካገኘጨረታውንበከፊልምሆነሙሉበሙሉየመሰረዝመብቱየተጠበቀነው፡፡
በስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የደቡብ
ምርጥ ዘር ድርጅት
ሀዋሳ