የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደመባ /007/12
መ/ቤታችን የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደሩ ኪራይ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፦
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ መካፈል የሚያስችል ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉንና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በአንድ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ «ኦሪጅናል» እና «ኮፒ» በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የየሎቱን ሰነዱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ከባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው::
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢየሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በየዲስትሪክቱ በተጠየቀው የማሽነሪ ብዛት ልክ የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ ከተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው።ከጨረታው ደንብና መመሪያው ውጪ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት
የፖ. ሳጥን ቁጥር 688
የስልክ ቁጥር 046-220-55-91/ 046-220-98-90
ፋክስ 046-220-23-66/046220-29-13
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን
ሀዋሳ ኢትዮጵያ