በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደመባ 02/01/2013
መ/ቤታችን የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር ኤክስካቫተር፣ ሮለር እና ሎደር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት የጨረታ ማስታወቂያ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ «ኦርጅናል» እና «ኮፒ» በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የየሎቱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 8 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው::
- አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስረከቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን
አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት
የፖ.ሣ.ቁጥር 688
የስልክ ቁጥር 046-220-55-91/046-220-98-90
ፋክስ 046-220-23-66/046220-29-13
ሃዋሣ ኢትዮጵያ
ደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን