የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2012 በጀት ዓመት የተለያዩ ግዥዎችን ማለትም፡
- ቋሚ እቃዎች
- አላቂ የጽህፈት እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች /ሳሙና /
- የደንብ ልብስ /የወንዶች ጫማ /
- የ ቧንቧና የኤሌክትሪክ ነክ እቃዎች
- የእጅ ሳኒታይዘር
በአገራችን ሰፊ ተነባቢነት ባለው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- በ2012 ዓም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የግብር መክፍ ያ ቁጥር /TIN/ያለው/ያላት/
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች።
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት / ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይቻላል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በማሰብ በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾን የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ኦርጅናሉን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 4 ፊት ለፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው specification ውጭ በመሰረዝ ወይም በማሳሳል ማቅረብና በሌላ ዋጋ ተንተርሶ መጫረት አይፈቅድም
- የጨረታው እሸናፊ በተሰጠ የጨረታ ሰነድspecification/መሰረት እቃውን ለማቅረብ ውለታ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ወስጥ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከታቸው የኮሌጁ ባለሙያዎች እየተረጋገጠ ለኮሌጁ ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅባታል:
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ፡ 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ቁጥር 12 ጨረታው ይከፈታል
- ኮሌጁ የቫት ሰብሳቢ መ/ቤት ስለሆነ 7.5% ቫት ቆርጦ ህጋዊ ደረሰኝ ይሠጣል።
- የጨረታ አሽናፊ የሚለየው በሎት ሳይሆን በነጠላ ዋጋ መሆኑን ኮሌጁ ያሳውቃል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ኢቁ 033-12-44-14/15/16
ፋክስ ቁ፤ 033-111-84-68
በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ
የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ደሴ