የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የ2013 በጀት ዓመት የተለያዩ ለመስሪያቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም
- ሎት አንድ ፡– ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች፣
- ሎት ሁለት፡– ኬሚካልና የኬሚካል እቃዎች፣
- ሎት ሦስት : የመካኒካል/ቧንቧ መፍቻ፣ መቁረጫ ፤የኤች ዲፒና የጂ ኤስ የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎች ፣
- ሎት አራት፡– የመኪና እቃ መለዋወጫ እቃዎች ፣
- ሎት አምስት፡– አላቂ የፅ/መሳሪያ እቃዎች፣
- ሎት ስድስት፡ የፅዳት እቃዎች ፤
- ሎት ሰባት ፡–የህትመት እቃዎች ፤
- ሎት ስምንት፡የሠራተኛ ደንብ ልብስ እቃዎች፣
- ሎት ዘጠኝ፡– የኤሌክትሪክ እቃዎችን፣
- ሎት አስር፡– ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት አስራ አንድ፡– የውሃ ፓምፕና ሞተር እቃዎች አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ማቅረብ የሚችል፣
- የግዥው መጠን ከ50,000.00/ሃምሳ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት የጨረታ ሃሳቡን ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት ተለያይቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ዶክሜንት የሚጠይቁ ሎቶችን ማለትም ሎት አስራ አንድ 1 ኦሪጂናል(ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ የያዘ ) እንዲሁም 1 ኮፒ (ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ የያዘ) በአጠቃላይ 2 ሰነዶችን እንዲሁም ቴክኒካል ዶክሜንት የማይጠይቁ ሎቶችን ማለትም ፣ ከሎት እስከ ሎት 10 በሁለት ፖስታ ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 01 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለጽን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን። ነገር ግን 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
- የጨረታ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ሲገለጽለት የውል ማስከበሪያ 10% ብር ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ ኣገልግሎት ጽ/ቤት ሮቢት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033-31215-83፤0913353221፤091460837 9 ፤0914 737410 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
የደሴ ከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት