ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2013 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት-1 ቋሚ ዕቃ
- ሎት-2 አላቂ ዕቃዎች
- ሎት-3 የሰራተኞች ደንብ ልብስ ፍራሽ እና ትራሶች
- ሎት- 4 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-5 የግንባታ ዕቃዎች
- ሎት-6 የስፖርት ዕቃዎች
- ሎት-7 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ሎት-8 የምግብ ዕቃዎች
ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር እንዲችል ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- ግዥው ከ50,000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-8 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ 100(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1 ፐርሰንት ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡
- ማንኛው ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ግ/ን/አ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወደ ቀጣዩ የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ጨረታው በእያንዳንዱ ፍላጎት በተናጠል ዋጋ ነው::
- አሸናፊው በገባው ውል መሰረት ዕቃዎችን እስከ ተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት
በስልክ ቁጥር 0333114684 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት