ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ጐንደር መስተዳደር ዞን የደራ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለደራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የአርብ ገበያ ጤና ጣቢያን ደረጃ ለማሣደግ
- ሎት 1 ሶስት/3/ ብሎክ የህንፃ ግንባታ የእጅ ዋጋ እና የቁሣቁሱን ጨምሮ
- ሎት 2 ለአጥር ግንባታ አገለግሎት የሚውል የግንባታ ቁሣቁስ
- ሎት 3 በኮይካ ፕሮጀክት ለሚገነባው አዳራሽ እና ቢሮ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለግንባታው ደረጃ ስምንት/8/ እና ከዚያ በላይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
- ግዡ ከብር 200 ሺህ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል::
- ከ1-4 ለተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖር ይገባል::
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎቱ 50 ብር በመክፈል ደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃ አቅርቦት በየሎት ምድቡ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው::
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን ዓይነት በመግለጽ ዘወትር በስራ ሰዓት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል:: 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል::
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582580141 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ::
የደራ ወረዳ ገን/ኢ/ል/ጽ/ቤት