ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎጃም ዞን ገን/ኢኮ/ት/መምሪያ የደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የዕቃ አቅርቦትና የአገልግሎት ግዥዎችን ማለትም፡-
- ሎት 1. የጽ/መሳሪያ እና አነስተኛ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 2. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ
- ሎት 3. የጽዳት/የንፅህና/ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 4. የውጪ ፈርኒቸር አቅርቦት ግዥ
- ሎት 5. የሀገር ውስጥ ፈርኒቸር አቅርቦት ግዥ
- ሎት 6. የመኪና ጎማ አቅርቦት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ አለባቸው
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝ መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 /ሃያ/ በመክፈል ከደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ለሞሉት ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በደምበጫ ዙ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በሚል ማስያዝ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ ከሞላ በኋላ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ፣ ስምና አድራሻ በማስቀመጥ ደም/ዙ/ወረዳ ገን/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
- የጨረታ ማስታወቂያው ወይም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- በተራ ቁጥር 9 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- መ/ቤቱ አሸናፊውን በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር አሸናፊ የሚለይ ይሆናል::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587730274 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገን/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት