ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደራችን ውስጥ ያሉ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የጽ/መሳሪያ፣
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 3 የማሽን ኪራይ
- ሎት 4 የጽዳት እቃ
- ሎት 5 የዉጭ ፈርኒቸር አቅርቦት ግዥ
- ሎት 6 የሀገር ዉስጥ ፈርኒቸር
- ሎት 7 ብትን ጨርቅ
- ሎት 8 የተዘጋጁ ልብሶች
- ሎት 9 የወንድና የሴት ጫማዎች
- ሎት 10 የደንብ ልብስ ስፌት አቅርቦት ግዥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ናምበር ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ግዡ ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው፡፡ ቫት የማይጠይቁትን ሎቶች ላይ ግን የቫት ተመዝጋቢ ያልሆኑትም ይወዳደራሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፣
- የሚገዙት የእቃ አይነቶች /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሚገዙበት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በገዙት ሎት ብቻ 1 በመቶ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
- የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ለሎት 1 ፣ ሎት 2 እና ሎት 3 ብር 50.00 ሲሆን ለሌሎች ሎቶች ብር 20.00 በመክፈል መግዛት አለበት፣
- ማንኛውም ተጫራች በገዛው የዋጋ መሙያ እስፔስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ ሳይኖርበት በመሙላት በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ስዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን ድረስ ማለትም እስከ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእንግዳ መቀበያ ክፍል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ 3፡30 ይከፈታል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሞላው ዋጋ ላይ ተተርሶ መሙላት አይቻልም፣
- ማነኛውም ተጫራች ባለው የስራ ፈቃድ መሰረት በሎት ውስጥ የሚፈልጉ ዕቃዎችን በሙሉ መሙላት አለበት ስለሆነም ሙሉ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከዉድድሩ ዉጭ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን አሸናፊ የሚለየዉ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ አድርጎ የሞላዉ ይሆናል፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውል በመያዝ በውላቸው መሰረት ዕቃውን ማቅረብ አለባቸው ፣
- ማንኛውም ዕቃ በራሱ ወጪ ሸፍኖ ደም/ከተ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለ12 ሴክተሮች በጠየቁት መሰረት ከተረጋገጠ በኋላ ገቢ ማድረግ አለበት ፣
- ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587730283 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
የደምበጫ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት