የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአብክመ ቴ/ሙ/ቢሮ በምዕ/ጐጃም ዞን በደምበጫ ከተማ አስተደደር የደምበጫ ቴ/ሙያ ኮሌጅ
- የጽህፈት መሣሪያ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፣
- የህንፃ መሣሪያ ዕቃዎችን፣
- የጋርመንት፣
- የግብርና፣
- አውቶሞቲቭ እና
- የICT ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ እንደሁም አስመጭዎች፣ የኮምፒውተር ዕቃዎችና ተዛማጅ ዕቃዎች አቅራቢነት የተሰማሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1.4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የዕቃወች ዓይነትና መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ/ በመክፈል ከግዥ ፋ/ይ/ን/አስ/ደ/የሥ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጫራታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በኮሌጁ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደምበጫ ቴ/ሙ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን እስከ ጠዋት 3፡30 ማስገባት ይችላሉ
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድራፍቲንግ ወርክ ሾፕ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ይከፈታል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ይከፈታል::
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በኮሌጁ ደረሰኝ መሠረት ማስያዝ አለባቸው::
- ኮሌጁ የሚረከባቸውን ዕቅዎች ይዘትና ጥራት በባለሙያ እንዲረጋገጡ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- የጫራታ አሸናፊዎች በሎት ወይም በተናጠል የሚለዩ ይሆናል
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር ዐ6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0587730418 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- ከዚህ በፊት የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የመለሱ ተጫራቾች ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ::
- የመጫራቻ ሰነዱ ጫራታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል::
- ግዥ ፈፃሚ መ/ቤቱ የተጠየቁትን ዕቃዎች በ20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አሸናፊው አቅራቢው ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ኮሌጁ ድረስ አጠቃሎ የማስገባት ግዴታ አለበት::
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም::
- በማንኛውም ሁኔታ ለሚፈጠር ችግር በአብክመ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሠረት የሚፈጸም ይሆናል::
ደንበጫ ከተማ ቴ/ሙያ ኮሌጅ