የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ፡
- ሎት1፡–የጽህፈት መሣሪያዎች
- ሎት2፡–የደንብ ልብስ፣
- ሎት፡-3-የተለያዩ ህትመቶች
- ሎት፡-4 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማሳተም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡
- በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው።
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ ዕቃዎችን እና የሚታተሙት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የዕቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን/ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ በይፋ ይከፈታል።ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 20/ ሃያ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጭ ወደ ጤና ተቋሙ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በኮፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-890-02-84/ 09-21 131228 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ