የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ሰሜን ሸዋ ዞን የያያ ጉለሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት የመንግሥት መ/ቤቶች ጥራቱን የጠበቀ የተለያዩ እቃዎች፡-
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የፅዳት መሣሪያዎች
- የደንብ ልብሶች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች/ፈርኒቸር
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች
- የተለያየ የሞተርና የመኪና ጎማዎች
በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን ጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው ለአቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- ማንኛውም የጥቃቅንና አነስተኛ እና ለሎችም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) 20,000 (ሃያ ሺ ብር) (በካሽ 20,000 Birr) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቢሮ ቁጥር 03 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 21 የሥራ ቀናት በመቅረብ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ዋጋው የትራንስፖርት፤ የማውረጃ ወጪ ጨምሮ የሚሸጥበትን በሰነዱ ላይ ተሞልቶ ይቀርባል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ፡ በ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ልክ በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0901069826 ወይም 0913757015 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር
ሰሜን ሸዋ ዞን ያያያ ጉለሌ ወረዳ
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት