የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 15 ት/ጽ/ቤት የየካ ቦሌ የመ/ጀ/ደ/ት/ቤት ለ2013 ዓም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት፡-
- የትምህርት ዕቃዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ፤ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋሉ፡፡
በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
1 ለተጠቀሱት ዕቃዎች በዘርፉ የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፡፡ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ያላቸው፡፡
- 1.1. ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጅናሉን በማመሳከር እያንዳንዱ ኮፒ ለየብቻ በአንድ ገጽ ላይ በማስነሳት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለበት፡፡
- 1.2 ተጫራቾች በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ድረገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- 1.3 ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ
- 1.4 ከ5000000 ብር በላይ የሚቀርብ ቫት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /ቢድ ቦርድ/የኢትዮጵያ ብር/3000/ ሶስት ሺ ብር / በባንክ የክፍያ ማዘዣ / ሲፒኦ ጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- 15 ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ 50 (ሃምሳ) ብር በመከፈል በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስባት አለባቸው፡፡
- 1.6 ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ 3 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይንም ሁለቱን ወይም መጫረት ይችላሉ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ሎት ዕቃዎች መራርጦ ለተወሰኑት ዕቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- 1.7 ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ(10) አሥር ተከታታይ የሥራቀናትከፍት ሆኖ በአስረኛው ቀን በ11 ሰአት ይታሸጋል በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ3፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- 1.8 ት/ቤቱ ጨረታውን ሰመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 1.9 ተጨማሪ ማብራሪያ የሚፈልጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0910158236 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የት/ቤቱ አድራሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ስሙ ጨሪ አካባቢ የካ ቦሌ የ/መጀ/ደ/ት/ቤት
የካ ቦሌ የ/መጀ/ደ/ት/ቤት