የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና መስኖ ኢነርጂ ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን ውሃ መስኖና ኢነርጂ መምሪያ የዓለም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት
- ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ፣
- የፅህፈት መሳሪያ፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- ፓናል ቦርድ ኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫ፣
- የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣
- ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ የደንብ ልብስ የተዘጋጁ፣ የደንብ ልብስ ጫማ፣ በ2013 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር ኮፒውን በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- የሞሉት ዋጋ ከ50,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
- ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ የጨረታ ሰነድ በብር 50/ሃምሳ ብር/ ሌሎች የተዘረዘሩትን ሠነዶች በ25/ ሃያ አምስት ብር/ ጨረታው ከወጣበት ቀን እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 01 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በመ/ቤታችን የውስጥ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመ/ቤቱን ስምና አድራሻ በመግለፅና በማሸግ በዓለም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ ሂደት ቢሮ ቁ. 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ሠዓት ታሽጐ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ግዥ ፈፃሚው አካል ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈፀሙ በፊት በጨረታ ሠነዱ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% /ሃያ በመቶ/ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ሙሉ እቃ በዓ/ከተማ ውሃ አገ/ሎት ፅ/ቤትባዘጋጀው መጋዘን ማስረከብ ይኖርበታል።
- በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 011-13-20-701/106/081 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻችን ከአዲስ አበባ 180 ኪሜ ከደብረብርሃን 130 ኪሜ መሆኑን እናሳውቃለን ::
ማሳሰቢያ፡-የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም ህዝባዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
በአ.ብ.ክ.መ መንግሥት ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ
የዓለም ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት