ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሽዋ ዞን የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በሀገር ውስጥ ገበያ በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ ከአምራችና ጅምላ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፡– ልዩ ልዩ የግብርና ኬሚካሎች/ፀረ–ነፍሳት፣ፀረ–አረምና ፀረፈንገስ/
- ሎት 2፡– ልዩ ልዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች
- ሎት 3፡– ልዩ ልዩ መገልገያ መሳሪያዎች/ማጭድ፣መርጫ መሳሪያ፣ትጥቅ ልብስና የነቀዝ ፒክስ/
- ሎት 4፡– ለእንሰሳት መኖ የሚውል ጥሬ ዕቃ /የዶሮ ኮንሰንትሬት/
- ሎት 5፦ ልዩ ልዩ ሰብሎች/ስንዴ፣ዱቤ ሽምብራ፣የአካባቢ ሽምብራ፣ባቄላ፣ አተርና ተልባ/ ሽያጭ
- ሎት 6፡– የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፉርሽካ) ሽያጭ
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በእነዚህ ንግድ ዘርፍ /ዘርፎች/ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዘገባ ያለው፡፡
- የበጀት ዓመቱ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን የታደሱ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
- ለእያንዳንዱ ሎት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል በወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላፊነቱ የተወሰነ ስም በአካውንት ቁጥር 1000082689967 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠባሴ ቅርንጫፍ በማስገባት እና ያስገቡትን የባንክ ደረሰኝ በመያዝ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ. ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ማግኘት ይችላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋው 2% /ሲፒኦ/ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ብርሃን ከተማ ባሉ ባንኮች በዩኒየኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ለያይቶ እና አሽጎ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዩኒዬኑ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት /ቅዳሜ እስከ 6፡30 ጨምሮ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት 7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በ7ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን እና ህዳሴ የመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላያተ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር፡– 0116816385/ 0116814115 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር ወደራ
ሁለገብ የገበሬዎች ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ኃላ/የተ. ደ/ብርሃን