የወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ.የተ.የግ. ማህበር
የተለያዩ ሸቀጦች ክምችትና ሥርጭት ማዕከል ግንባታ
የጨረታ ማስታወቂያ
የወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ላይ የተለያዩ ሸቀጦች ክምችትና ሥርጭት ማዕከል ግንባታ ለማስገንባት ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሥገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት :
- ደረጃቸው GC 5/BC-5 እና ከዛ በላይ የሆኑ ፈቃዳቸውንና የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ከኮንስትራክሽን ሚንስቴር ያወጡና ለ2012 ዓ.ም ያሣደሱ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ከኩባንያው ፋይ/ንብ/አስ/መምሪያ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ ዶክመንት 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም ባንክ ዋስትና ለአንድ መቶ አስራ ስምንት ቀናት (18 calendar days) ከቴክኒካል ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ኩባንያው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር ፦ አዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት 011 552 1009/011 869 3979
የወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር