ግልጽ የጨሬታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደ/ጎንደር ዞን የወረታ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን/ በUIIDP በጀት የወረታ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤ/ኮ/ጽ/ቤት ከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ UIIDP የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ለቢሮ አገልግሎት የሚውል፡-
- ሎት-1 የጽህፈት መሣሪያ ፤
- ሎት-2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው፤
- የግዥው መጠን ከ200 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት የተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/አምሳ ብር/ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ በመክፈል ወ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 21 መግዛት ይችላሉ ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፤
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱንና ንግድ ፍቃዱ በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወረታ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ መግዛትና ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ6፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል::
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የብዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ብዛቱ 20 በመቶ ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል::
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃውን ወረታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት::
- ውድድሩ በጥቅል ነው::
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-446-1345 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- አጠቃላይ የውል ሁኔታ በተመለከተ ወይም የተጫራቾች መመሪያ (instruction to bid) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አታች አድርገናል::
የወረታ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት