Consumable Goods / Firewood / Foodstuff and Drinks / Products and Services

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጤፍ ፣የዳቦ ዱቄት፣ ስጋ፣ ሩዝ፣ፓስታ፣የአጃ ቅንጬ ፣ድንች፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቀይ ሽንኩርት፣ቃሪያ፣ቲማቲም፣ ምጥን በርበሬ፣ ምጥን ሽሮ፣ እርድ፣ የዳቦ እርሾ፣ የሻይ ቅጠል፣ምስር ክክ፣ አተር ክክ፣የአይወዲን ጨው፣እና ጎመን ዘር እና የማገዶ እንጨት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

 የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ወዩ////03/2013

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2013 ዓም በሚፈቀድ መደበኛ እና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውሉ ፤ጤፍ ፣የዳቦ ዱቄት፣ ስጋ፣ ሩዝ፣ፓስታ፣የአጃ ቅንጬ ፣ድንች፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቀይ ሽንኩርት፣ቃሪያ፣ቲማቲም፣ ምጥን በርበሬ፣ ምጥን ሽሮ፣ እርድ፣ የዳቦ እርሾ፣ የሻይ ቅጠል፣ምስር ክክ፣ አተር ክክ፣የአይወዲን ጨው፣እና ጎመን ዘር እና የማገዶ እንጨት በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው የሚገዛቸው እቃዎች ከዚህ በታች ባሉት ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡

 1. ሎት 01 /አንድ/ – የባልትና ውጤቶች
 2. ሎት 02 /ሁለት/ – የፋብሪካ ውጤቶች
 3. ሎት 03 / ሶስት/ የእንስሳት ተዋጽኦ
 4. ሎት 04 /አራት/ – አትክልት ተዋጽኦ
 5. ሎት 05 / አምስት/– ጤፍ
 6. ሎት 06 /ስድስት/—– ጎመን ዘር
 7. ሎት 07/ሰባት/ የዳቦ ዱቄት
 8. ሎት 08/ስምንትየማገዶ እንጨት

3 ጊዜ የወጣ ሲሆን በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፣፡

በመሆኑም፡

 1. ተጫራቾች በየምድቡ በስራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ የሚችሉ፣በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፣ እንዲሁም በማህበራት የተደራጁ ከሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ /ቤት ኃላፊ ፊርማ ብቻ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በባለሙያ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የንግድ ስራ ፈቃድ ቲን ነምበር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የድጋፍ ደብዳቤ ሲፒኦና የመሳሰሉት መረጃዎች ተጨምሮ በጥሩ አስተሻሸግ በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ከሎት አንድ እስከ ሎት 7 ያሉትን 100.00/ አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ገዝተው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ በማህበራት የተደራጁ ከሆኑ ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት አንድ እስከ ሎት ስምንት ድረስ ብር 50,000.00/ ሃምሳ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO/ የባንክ ጋራንቲ/ ከጨረታ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም/የተከለከለ/ነው፡፡ 
 4. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጀው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ስራዎች ማስፋፊያ ጽ/ቤት ብቻ በጽ/ቤት ኃላፊው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ 
 5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን የምግብ ጥሬ እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎች የማውረጃና የመጫኛ ወጪዎችን ሸፍነው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶ በር ዋናው ግቢ እና ሰመረሳ ካምፓስ ግብርና ግቢ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 6. ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ21/12/2012 ጀምሮ እስከ 05/13/2010 ከቀኑ 7፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲፋይናንስና በጀት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ክፍያውን በመክፈል ግዥ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስ/ር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 04/1/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማለትም ከሎት አንድ እስከ ሎት 7 ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በንግድ ማእከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይታገድም፡፡ 
 7. ተጫራቾች ከሎት አንድ እስከ ሎት ስምንት ድረስ የምግብ ጥሬ እቃ ኦርጅናል ዶክመንት እና ከላይ በተራቁጥር አንድ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለይተው ከፖስታው ላይ በመጻፍ ለየብቻ በጥሩ አስተሻሸግ በመታሸግ መቅረብ ያለበት ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያው ከኦርጅናል ፖስታው ውስጥ አብሮ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ በተጨማሪም ምንም አይነት ዶክመንት በእጅ ይዞ መቅረብ አይቻልም፡፡ 
 8. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡ 
 9. ተጫራቾች በሁሉም የመወዳደሪያ ሰነዶች ገጽና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማተም በመፈረም በጥሩ አስተሻሸግ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። 
 10. ማንኛውም ተጫራች በተለያዩ ምክንቶች ውሉን ማቋረጥ ቢፈልግ ከሶስት ወር በፊት ለዩኒቨርሲቲው በጽሁፍ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ 
 11. ጨረታው ከተከፈተ አንስቶ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን ሲፒ.ኦና ጋራንት ሲያሰሩ ለ18/አንድ መቶ አስራ ስምንት/ ቀናት መሆን አለበት፡፡ 
 12. ተጫራቾች ጨረታው ለ1/አንድ አመት /የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ማሻሻያ የሚደረገው የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ አቅርቦት 50% /ሃምሳ ፐርሰንት/ ከአቀረቡ በኋላ በሚመለከተው ክፍል ማቅረባቸው ሲረጋገጥ በግዥ መመሪያው በተቀመጠው ቀመር አሰራር እና ማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በሚያቀርበው የዋጋ ጥናት መሰረት ከጨመረ የሚጨምር ከቀነሰ የሚቀንስ ሲሆን፤ ቀሪውን 50% ሃምሳ ፐርሰንት/ አንድ ጊዜ በተስተካከለው የማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ዋጋ ብቻ የሚያቀርሱ መሆኑን አውቀው መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ማለት ውል ከገቡ በኋላ 50% /ሃምሳ ፐርሰንት/አቅርበው ሲጨርሱ ብቻዋጋው ይሻሻላል እንጂ ከዚያ በፊት ማሻሻያ መጠየቅ አይቻልም፡፡ 
 13. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የምግብ ግብዓቶች በሌሎች ተቋማት ተወዳድረው የሚያውቁና የመልካም ስራ አፈጻጸም በሚመለከተው ኃላፊ የተፈረመ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይመረጣል፡፡ 
 14. ተጫራቾች የእንጨት ጨረታን በተመለከተ ምንም አይነት የዋጋ ማሻሻያ አይደረግለትም ማለትም መጀመሪያ ሰሞላው ዋጋ ጠቅላላ አቅርቦቱን እንደሚያቀርብ አውቆ መወዳደር ይኖርበታል፡፡ 
 15. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫት የሚመለከታቸውን ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት እና የመጫኛና ማውረጃ የጉልበት ዋጋ ጨምሮ መሙላት አለበት ፤ ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበው ዋጋ ሁሉንም ወጪ ኣካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡ 
 16.  ተጫራቾች የምግብ ግብዓት ኣቀራረብን በተመለከተ መቼና እንዴት ማቅረብ እንዳለባቸው ከዋጋ መሙያ ጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተቀመጠ ስለሆነ በጥንቃቄ  አንብብውና አይተው መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 17.  ስርዝ ድልዝ ያለበት የዋጋ መሙያ ስርዝ ድልዝ ያለበት ተራ ቁጥር ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ 
 18. ዩኒቨርቨርሲቲው የሚገዛውን የምግብ ግብዓት 20% የመጨመርና የመቀነስ እንዲሁም ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 19. በተጨማሪም ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ዩኒቨርሲቲው በሚሰጠው ትዕዛዝ አማካይነት ጭምር ይሆናል፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 540 21 86 /033 431 15 44 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

 የወልድያ ዩኒቨርሲቲ