Computer and Accessories / Generators / Laboratory Equipment and Chemicals / Motors and Compressors / Pumps / Water Engineering Machinery and Equipment

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም የአይሲቲ መሰረተ ልማት የሚያስፈልጉ የአይሲቲ እቃዎች፣ጀኔሬተር፣ የውሃ ፓምፕ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ወዩ////04/2013

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2013 . በሚፈቀድ መደበኛ እና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውሉ፤ የአይሲቲ መሰረተ ልማት የሚያስፈልጉ የአይሲቲ እቃዎች፣ ጀኔሬተር እና የውሃ ፓምፕ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው የሚገዛቸው እቃዎች ከዚህ በታች በሎት ተዘርዝረው ቀርበዋል።

 1. ሎት 1/አንድ/ የአይሲቲ መሰረተ ልማት የሚያስፈልጉ የአይሲቲ እቃዎች
 2. ሎት 2/ሁለት/ – –ጀኔሬተር
 3. ሎት 3/ሦስት/ –የውሃ ፓምፕ

ሲሆን በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

በመሆኑም፦

 1. ተጫራቾች በየምድቡ በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝር፤ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት ያላቸው፣ እንዲሁም በማህበራት የተደራጁ ከሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ /ቤት ኃላፊ ፊርማ ብቻ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በባለሙያ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት አይኖረውም:: ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ፋይናንሽያል ዶክመንት ለብቻ ቴከኒካል ዶክመንት የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ቲን ነምበር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፊኬት፤ የድጋፍ ደብዳቤ፤ ሲፒኦና የመሳሰሉት መረጃዎች ተጨምሮ ከቴክኒካል ኦርጅናሉ ጋር ለብቻ በጥሩ አስተሻሸግ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
 2. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ቴክኒካል ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ኮፒ፣ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ለሎት አንድ፤ ለሎ ሁለት እና ለሎት ሦስት 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል እንዲሁም በማህበር የተደራጁ ከሆኑ ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ ዳይሬክቶሬት ሙግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት አን እስከ ሎት ሦስት ብር 50,000,00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO(የባንክ ጋራንቲ) ከቴክኒካል ዶክመንት ሰነዶች ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም/የተከለከለ ነው።
 5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋማቱን ከአደራጀው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ሥራዎች ማስፋፊያ /ቤት ብቻ በጽ/ቤት ኃላፊው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
 6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎች የማውረጃና የመጫኛ ወጪዎችን ሸፍነው የሚገጣጠሙትንም በመገጣጠም ስልጠና የሚያስፈልጋቸውንም ስልጠና በመስጠት ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶ በር ዋናው ግቢ ንብረት ከፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል::
 7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 18/02/2013 . ጀምሮ እስከ 02/3/2013 . ከቀኑ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስ/ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስ እስከ 02/3/2013 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማለትም ከሎት አንድ እስከ ሎት ሦስት ማስገባት ይችላል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በንግድ ማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም
 8. ከሎት ኣንድ እስከ ሎት ሦስት ድረስ እቃዎች የቴከኒካል ኦሪጂናል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጂናል ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማዘጋጀት ዝርዝር የእቃው ስፔስፊኬሽን/የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ ቲን ነምበር (የግብር ከፋይመለያ ቁጥር) የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርትፊኬት፣ ሲፒኦና፤ ቃለ መሃላ፤ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፤ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የመሳሰሉት መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን፤ ተጨምሮ/ለብቻ በጥሩ አስተሻሸግ በመታሸግ መቅረብ አለበት፡፡
 9. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
 10. የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉ እና የተመረጡ አቅራቢ ድርጅቶች ለዋጋ ውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡ በሁሉም የማወዳደሪያ ሰነዶች ገጽና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማተም በመፈረም በጥሩ አስተሻሽግ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 11. ጨረታው ከተከፈተ ኣንስቶ 90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን ሲፒኦ ሲያሰሩ 118 (አንድ መቶ አስራ ስምንት ቀን) አድርገው ማሰራት ይጠበቅባቸዋል
 12. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት እና የመጫኛና ማውረጃ የመገጣጠሚያና ስልጠና የሚያስፈልግ ከሆነ የማስልጠኛ ዋጋን ጨምሮ መሙላት አለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበው ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
 13. ስርዝ ድልዝ ያለበት የዋጋ መሙሊያ ስርዝ ድልዝ ያለበት ተራቁጥር ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
 14. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 033 540 21 86 /033 431 15 44 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ