Building Construction / Wood and Wood Working

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በሚፈቀድ መደበኛና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት ማስቀመጫ ሸድ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ወዩ////06/2012

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ 2013 . በሚፈቀድ መደበኛና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው

 • ለተማሪዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት ማስቀመጫ ሸድ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

በዚህ መሰረት :

 1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ የተሰማሩ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ የግንባታ ሥራ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም በማህበራት የተደራጁ ከሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ /ቤት ኃላፊ ፊርማ ብቻ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በባለሙያ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት አይኖረውም። ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ቴክኒካል አርጂናል ቴክኒካል ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናል ፋይናንሻል ኮፒ በማለት የንግድ ሥራ ፈቃድ ቲን ነምበር የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የድጋፍ ደብዳቤ ሲፒኦና የመሳሰሉ መረጃዎች ተጨምሮ ለየብቻ በጥሩ አስተሻሸግ በመታሸግ መቅረብ አለበት።
 2. ተጫራቾች ኦርጂናል ዶክመንትና ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ አሽገው በአንድ ፖስታ በጥሩ አስተሻሸግ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. የማገዶ እንጨት ማስቀመጫ ሸድ ጨረታውን ለመሳተፍ የሚችሉት ከደረጃ – -9 BC OR GC መሆናቸው ይታወቅ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረ ሰነዶቹን፧ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል እንዲሁም በማህበር የተደራጁ ከሆኑ ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 5. ተጫራች ለግንባታው አስፈላጊውን እቃና ሠራተኞች አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሽያል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ስመለየትና የጨረታ ማስከበሪያዎችን በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 6. ተጫራቾች ፋይናንሽያል ኦርጅናል ፋይናንሽያል ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል ቴክኒካል ኮፒውን አራቱንም ፖስታ በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ  ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) የባንክ ጋራን/ ከቴክኒክ ዶከመንት ሰነዶች ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም (የተከለከለ) ነው።
 8. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትከ ተቋማቱን ከአደራጀው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ሥራዎች ማስፋፊያ /ቤት ብቻ በጽ/ቤት ኃላፊው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
 9. አሸናፊው ድርጅት ሙሉ ወጪውን አጠቃሎ ሥራውን ይሸፍናል፡፡
 10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንጋዜጣ ከወጣበት ቀን 18/2/2013 . ጀምሮ እስከ 8/3/2013 . ከቀኑ 1130 ሰዓት ድረስ 21 ቀን ይቆያል፡፡ የጨረታ ሰነዱን ወል ድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስ/ ዳይሬክቶሬት ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 8/3/2013 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላል። የጨረታ ሳጥኑ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በንግ ማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም
 11. የቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማዘጋጀት (ዝርዝር የሥራውን እስፔሲፊኬሽን) የንግድ ሥራ ፈቃድ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ቲን ነምበር የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፤ የገቢዎች ጉምሩክ ክሊራንስ የድጋፍ ደብዳቤ ሲፒአና ቃለ መሀላ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኢትዮ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የመሳሰሉት መረጃዎች ዋናውን እና ኮፒውን፤ ተጨምሮ ለብቻ በጥሩ አስተሻሸግ በመታሸግ መቅረብ አለበት፡፡
 12. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
 13. ተጫራቾች በሁሉም የመወዳደሪያ ሰነዶች ገጽና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማተም በመፈረም በጥሩ አስተሻሸግ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 14.  ጨረታው ከተከፈተ አንስቶ 90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን፤ CPO (ጋራንት) ሲያሠሩ ለ118 ቀን (ለአንድ መቶ አስራ ስምንት ቀን) መሆን አለበት፡፡
 15. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታከለ ዋጋ ጨምሮ መሙላት አለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበው ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
 16. ተወዳዳሪዎች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው ተጠንቅቀው መሙላት  አለባቸው፡፡ ስርዝ ድልዝ ከውድድር ውጪ ስለሚያደርግ ካለም ፓራፍ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
 17. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-033 431-15-44 ወይንም 0335402186 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ