ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ ግልጋሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የተለያዩ መድሃኒቶች ፣
- ሎት 2 የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና
- ሎት 3 የባለሞያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ ስፌት ለማሰፋት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበት የስራ ዋጋ ድምር 10 ሺህ ብር በላይ ከሆነ 2 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት ይሰበስባል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት ስራዎች 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የስራ ዋጋ 1 በመቶ በጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈፃፀም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 2 ያሉትን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከ16/02/2013 ዓ.ም እስከ 07/03/2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ22 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ07/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ ቁጥር 0333310252 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- ውድድሩ ከሎት 1 እና ከሎት 2 ውጭ በሎት ድምር ነው፡፡
የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል