የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር wku 08/2012
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2010 በጀት ዓመት ቲቺንግ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህሙማን አገልግሎት የሚውል የኮረና ቫይረስ (ኮቪድ 19) መመርመሪያ መሣሪያ ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- ሎት 1. ለቲቺንግ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) መመርመሪያ መሳሪያ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር… 80,000
በዚሁ መሠረት ተጋባዥ ተጫራች ድርጅቶች:
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማያያዝ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም ተጫራቾች ከግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገፅ ላይ የአቅራቢነት ፍቃድ የተመዘገባችሁበት የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዱ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ውስጥ በተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለመግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ቴክኒካል ዶክመንት ዋናውና 2 ኮፒ በተለያየ ፖስታ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የነጠላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ወልቂጤ ጉብሬ ክ/ከ/በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8:00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡የጨረታ ቴክኒካል ዶክመንት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሚያመቻቸው አዳራሽ በዚሁ እለት ከሰዓት በኋላ 8:30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ ፋይናንሽያል ዶክመንት የሚከፈትበት ወቅት የቴክኒክ ግምገማው እንደተጠናቀቀ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በተጠየቀው ለእያንዳንዱ ሎት መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፈርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የመንግስት የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱትን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0113220118 እና 0113220228 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ