ለሁለተኛ ጊዜ የሂሳብ ምርመራ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የማስታወቂያ ቁጥር 003/2012
የወላይታ ዳሞታ ገበሬዎች ኅ/ሥ/ ዩንየን የፋይናንሻል ስራ እንቅስቃሴ ከሐምሌ 1/11/2010 ዓም እስከ 30/10/2011ዓ.ም ድረስ ያለውን የአስራ ሁለት ወራት ደጋፊ ሰነዶችን የያዘ ቦክስ ፋይል ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም አዲት አድራጊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች፡
- የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፈቃድ ያገኘና የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
- በአገርቱ ሕግ መሰረት የኦዲት ሥራን ለማከናወን የሚያስችል ወቅታዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መልያ ቁጥር ያለው፣
- የኅብረት ሥራ ማህበራት ሂሳብ ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ኅብረት ሥራኤጀንሲ ወይም ከሌሎች ሕጋዊ አካላት ሥልጠና የወሰደና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- ተወካይ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪው ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የኅብረት ሥራ ማህበራት ሂሳብ የመረመረ ቢቻል ፒስትሪ አካውንቲንግችሎታ ያለው፣
- የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሂሳብ ለመመርመር ብቁ ባለሙያዎችን ሥራ ላይ ማሠማራት የሚችል ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚከሰተው ማንኛውም ኪሳራናችግር አስቀድሞ ኃላፊነቱን የሚወስድ፤
- ስራውን ለማጠናቀቅየሚፈጀውን ጊዜ እናዋጋበመግለጽ ዋጋ በመሙላት የሚያቀርብ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ሶዶ ማርያም ቤ/ክርስትያን ጀርባ አቶና ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት መንገድ ላይ በሚገኘው መ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ከላይ የተገለጹትንና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በማያያዝ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሳጥን በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911860440/0927000160 /0465510642 ኢሜል አዲራሻ meskdwfcu@gmail.com
የወላይታ ዳሞታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ