ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር ወሶዩ ግ.ጨ. 04/12 የተገለጹ ግንባታዎችን
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰሩ ደምቱ ፍልውሃ ቱሪስት መዳረሻ ማዕከል የተለያዩ ግንባታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል::
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው:-
- በዘርፉ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፊኬት፣ በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ እና ተጫራቾች በኤጀንሲው ድረ ገጽ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሥራ ተቋራጭነት ሥራ እንዲሰራ በሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተሰጠውን ደረጃ የተጠየቀውን GC-4 and above እና መልካም የሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::
- ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ እና በአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ ስድስት ኪሎ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በመቅረብ እያንዳንዱን ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢት/ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000018182789 በዩኒቨርሲቲው ስም በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ ይሁንና የጨረታው መክፈቻ ሥነ–ሥርዓት የሚካሄደው በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ብቻ ይሆናል ::
- ማንኛውም ተጫራች የሥራ ሳይት ማየት ካለበት ከውድድሩ በፊት በራሱ ወጪ ማረጋገጥ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመካፈል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO/ BANK GuRANTY ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታዎች በ21ኛ ቀናቸው በሠንጠረዥ ላይ እንደተገለጸ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
ተ.ቁ
|
የግንባታዎች ዓይነት |
የግን.መ. ቁጥር |
የሚጠይቀው ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
ግንባታዎች የሚከናወኑበት ቦታ |
01 |
Construction of Spring Cappe, Swimming Pool, Shower Room, Cafeteria, kitchen, Culvert, Cobble Stone and Checkerd, Flood Protect(Retaining Wall) Structures in Dimitu Town, Duguna Fango Woreda, Wolaita Zone
|
04/12 |
GC -4 and Above
|
150,000.00 |
ድምቱ ከተማ |
7. የመጫረቻ ሰነዱ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋቸውን ድምር በሚነበብ ጽሑፍ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻልና የቴክኒካል ኦርጅናሉን እና እያንዳንዳቸውን ሁለት ኮፒዎችን ለየብቻ በማሸግ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመጻፍ እስከ 21ኛ ቀን ድረስ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማስገባት አለባቸው :: ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት የለውም ::
8. የሥራው ዲዛይን ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ የቀረበ ስለሆነ ማየት ይቻላል ::
9. ኣሸናፊው ተጫራች ውል ከፈረመ በኋላ ለተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል ::
10. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 046551-46-15 ወይም 0911014555 ፋክስ 0465515113
ማሳሰቢያ ፡– የጨረታ ሠነዱን ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ
- በአዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ ስድስት ኪሎ ሽሮ ሜዳ አካባቢ
ስልክ ቁጥር – 0913790195 / 0912881430
በኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ