Audio Visual / Building and Finishing Materials / Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Computer and Accessories / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Photography and Filming Service and Equipment / Printing and Publishing / Wood and Wood Working

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም ለ2013 በጀት ዓመት ከሐምሌ 01/2012 እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም ድረስ በሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት እቃዎችን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

 

ግልፅ  የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 

የወላይታ ሶዶ ማረሚያ ተቋም ለ2013 በጀት ዓመት ከሐምሌ 01/2012 እስከ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም ድረስ በሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዓይነት እቃዎችን

 • ሀ. የሕግ ታራሚዎች መኖ እህል ዓይነቶች፣
 • ለ.የሕግ ታራሚዎች መኖ ምግብ ማጣፈጫዎች፣
 • ሐ. የመኖ ምግብ ማብሰያ ማገዶ እንጨት፣
 • መ. አጥንት የሌለበት ቀይ የከብት ሥራ፣
 • ሠ. የተለያዩ የቢሮ ጽሕፈት መሣሪያዎች፣
 • ረ. ከ5ኛ እስከ 12ኛ እስከ ተማሪዎች መማሪያና ማስተማሪያ እቃዎች እንዲሁም ማጣቀሻ መጽሐፍት፣
 • ሰ. የጉልበት ሠራተኞችና የሐኪሞች የሥራ ልብስ ማንቺንና ነጭ ገዋን የሚሰፋበት የብትን ጨርቅ እና የተዘጋጁ የሥራ ቱታዎች፣
 • ሸ. የተለያዩ የቢሮ የጽዳት እቃዎች
 • ቀ. የተለያዩ የመብራት እቃዎች በ. ለመ/ቤቱ ዙሪያ አጥር፣ የባህር ዛፍ ግድግዳ፣ ማገር፣ መሪ ተ. ለታራሚዎች ለተለያዩ ሥልጠና የሚውሉ፣ ብረታ ብረት፣ ግንባይኝነት፣ ብሎኬት ሥራና ለአናጽነት የሚያገለግሉ፣ ቱቡላሬ/ ላሜራ ኤሌከትሮድ፣ አሸዋ፣ ድንጋይ/ ሲሚንቶ፣ ቀለም፣ ኮላ፣ ስቱኮ/ሚስማር የባህርዛፍ ውጤቶች፣ የተለያዩ አይነት ቆርቆሮች እና ሌሎችን የሕንፃ መሣሪያዎች፣
 • ቸ. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና መሣሪያዎች፣ ኮምፒዩተር ከነፕሪንተርና ፕሮጀከተር የመሣሰሉትን፣
 • ኀ. ፈርኒቸር/ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣
 • ነ. ለታራሚዎች ሥልጠና የሚውሉ የተለያዩ የእንጨት ውጤቶች፣ ጣውላዎች፣ ኮምፔርሳቶዎች፣ ፋይዜቶችና ሌሎች ለሥራው የሚያገለግሉ እቃዎች፣ ሲሆን በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ነጋዴዎችን እና ከአደራጅ መ/ቤት የብቃት ማረጋገጫ ድጋፍ ያላቸውን የፋይናንስ ደንብና መመሪያ አሟልተው የሚቀርቡ የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን ጨምሮ በማጫረት ከአሸናፊዎች ጋር ውሉ ተዋውሎ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ለአሸናፊው ግን ከውል ማስከበሪያ ዋስትና ጋር የሚታሰብ ለመኖ እህል ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ከላይ ለተዘረዘሩ ለሌሎች ለእያንዳንዳቸው እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመለሰከረለት ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ ከየጨረታው ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ በፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 1. ተጫራቾች ለሁሉም ጨረታዎች የተዘጋጀውን የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከመ/ቤታችን ቢሮቁጥር 3 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ለ15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት አለባቸው፡፡
 2. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% አሸናፊነቱ በተረጋገጠ በ10 ቀናት ውስጥ በአሸናፊው እቃ አይነት ባሸነፈው ዋጋ ሰልቶ 10% ለማስያዣ ፈቃደኛ ካልሆነ እና አሸንፎም አላቀርብም ካለ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ገንዘበ ሙሉ በሙሉ ለመንግሥት ውርስ ይደረጋል፡፡
 3. ከላይ ከፊደል ተራ ሀ እስከ ነ ድረስ የተዘረዘሩ ዕቃዎች አይነት፣ መለኪያና መጠን/ብዛት ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በዝርዝር ተካቶ ይቀርባል፡፡
 4. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
 5. ተጫራቾች ለተዘረዘሩት እቃዎች በውድድሩ ቀን ናሙናሙን ይዞ መቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውንና የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ በጨረታው ሣጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ሁሉም እቃዎች ጨረታ ሳጥን ተዘግቶ የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ላይ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት 2፡30 ሰዓት እስከ 7፡30 ሰዓት ድረስ በተቋሙ ቅጥር ግቢ በቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ተጨምሮ በ7፡35 ሰዓት ተዘግቶ ሁሉም ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ግን ዕለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ 
 8. የእህል ተጫራቾች ለመ/ቤታችን የእቃዎች ማከማቻ መጋዘንና ቦታ ስለሌለው የቀጣዩን ወር በገባ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ተጠቃሎ ገቢ ሲያደርጉ የቀድሞ ወር ክፍያው ግን ወር በገባ እስከ 28ኛው ድረስ የሚፈጽም መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ ዓይነት በራሳቸው ማጓጓዣ በማምጣት በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ የማስከረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
 10. አሸናፊ አቅራቢዎች በዕቃዎች አቀራረብ ላይ የጥራትና የማስተጓጐል ችግር ቢፈጠር ለውል ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከመቀጣቱም በተጨማሪ ለተፈጠረው ችግር በሕግ ፊት ተጠያቂ ይሆናል፡፡
 11. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ/ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክቁጥር፡-0465512177/0916107578 ይጠይቁን፡፡

በደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ መንግሥት በፍትህና ፀጥታ 

ቢሮ በማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የሶዶ 

ማረሚያ ተቋም