የጨረታ ማስታወቂያ
የወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 ዓ.ም የበጀት ዘመን የተለያዩ የማስተማሪያ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የአገል/ሠራተኞች የሥራ ልብስ
- ልዩ ልዩ የቢሮ ዕቃዎችና አነስተኛ መሣሪያዎች
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- አላቂ የትምህርት መሣሪያዎች
- የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች ናቸው።
በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተለውን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
ሀ/ በዘመኑ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
ለ/ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
ሐ/ ተወዳዳሪዎች የሚፈለግበትን የባለቤትነት መረጃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
መ/ተጫራቾች የእጽዋት ዘር የጥራት ማረጋገጫ የድጋፍ ደብዳቤ ከግብርና ሚኒስቴር/ ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ማቅረብ የሚችሉ::
ሠ/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር) በCPO በቅድሚያ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
ረ/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሸ/ ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ከወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ በማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) ሰነዱን ከ20/12/2012 ዓም እስከ 3/13/2012 ዓም. ቀን እስከ 11:30 ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
በ/ ጨረታው ከ04/13/2012 ዓ.ም. እስከ 6፡30 ሠዓት በይፋ ይታሽጋል። ጨረታው 04/13/2012 ቀን 8:30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
ተ/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011341-24-95 በመደወል ይጠይቁ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወሊሶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ