የሕፃናት ማቆያ ማዕከል መገልገያ ዕቃዎች ግዥ
ድጋሚ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ኮ/ስ/ተ/ባ – ግ/ጨ/004/2012
የኮንስትራከሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን በ2012 በጀት አመት አዲስ ለሚያደራጀው የህጻናት ማቆያ ማዕከል የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ አይነትና ብዛት ያላቸውን የመገልገያ ዕቃዎችና ግብአቶችን ማለትም ፈርኒቸሮችን ለንጽህና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችንና፣ የመመገቢያ ዕቃዎችን፣ የኤለክትሮኒክስ ዕቃዎችን…..ወዘተ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ :-
ተ.ቁ |
ምድብ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታው ማስከበሪያ |
ምርመራ |
1 |
ሎት 1 |
ለህፃናት ማቆያ የሚሆኑ ፈርኒቸሮች፣ የመቆያ ክፍል ማስዋቢያ፣ መገልገያ እና የህጻናት መጫወቻ ዕቃዎች አልባሳት፣ የሕክምና ዕቃዎች፣ የንፅህና አላቂ የፅዳትና መመገቢያ ዕቃዎች |
5000.00 |
*ናሙና መቅረብ አለበት * እንደ አስፈላጊነቱ የቴክኒክ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ ሊያደረግ ይችላል
|
2 |
ሎት 2 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች /ቲቪ፣ፍሪጅ…/ |
የተዘረዘሩ የህጻናት መዋያ መገልገያ ዕቃዎችን ለማቅረብ ከሥራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት፣ ሙሉ አቅምና ብቃት ያላቸውን ድርጅቶችን በድጋሚ በጨረታ ለመግዛት ለውድድር ይጋብዛል ፡፡
በዚሁም መሠረት ተጫራቾች :-
11. በየዘርፉ በቀጥታ የተሰማሩ ሆነው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number) የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት /Tax clerance Cetificate/ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
12. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ኦሎምፒያ ዝቅ ብሎ፣ ከጌቱ ኮሜርሽያል ህንፃ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን የግዥ ቡድን ቢሮ 4ኛ ፎቅ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
14. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000 (አምስት ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚቻለው ጨረታው ከሚከፈትበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባለው ጊዜ ውስጥ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡
15.ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ አየር ላይ ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ለ15 ተከታታይ ቀናት በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
16. ተጫራቾች ይህንን ጨረታ በተመለከተ አማራጭ ዕቃና አማራጭ ዋጋ ማቅረብ በፍፁም አይኖርባቸውም፡፡
17. ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ክፍል 6/ስድስት/ ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በዝርዝር ናሙና ለተጠየቁባቸው የመገልገያ ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ናሙናው መቅረብ ወይንም ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ስለሆነ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ናሙናም ሆነ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
18. ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 መ/ቤቱ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
19. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት ሥራ የማይኖርበት መሆኑ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ከተገለፀ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
20. የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
የቢሮ ስልክ : 0115575960/ ፋክስ: 011554-12-68 /, ፖ.ሣ.ቁ 24134 /1000
አድራሻ : ገዥ ቡደን , 4ኛ ፎቅ 04-009,0115153357,
ሸዋ ዳቦ ሬት ስሬት , ከኦሎምፒያ
ዝቅ ብሎ፣ ከጌቱ ኮሜርሽያል ህንፃ ከፍ ብሎ
የኮንስትራክሽን ሥራዎች ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን
ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ