የጨረታ ማስታወቂያ
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚገኝ የባህር ዛፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡
- ከላይ ለተጠቀሰው አግባብነት ያለው ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ወይራ ሰፈር ወደ ቤተል መውጫ በስተግራ የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ፅ/ ቤት በመገኘት የማይመለስ 50.00 ሃምሳ ብር/ በመክፈል በዘርፉ ለመሰማራታቸው የሚገልፅ ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2000.00 /ሁለት ሺ ብር/ በየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት አድራሻቸውን በመግለፅ ወይራ ሰፈር የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሠጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- ት/ቤቱ ለግዥው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-0113696814
አድራሻ ፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የማነብርሃን ሁለተኛ
ደረጃ ት/ቤት ወይራ ሰፈር አደባባይ ፊት ለፊት
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ትምህርት
ጽ/ቤት የማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት