የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
(ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)
የጨረታ ቁጥር 02/2013
የካ /ዋ/ስ/አ/ጽ/ቤት በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን የ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት1 ፡– 1ኛ ደረጃ አገር አቋራጭ 65 ሰው የሚይዝ አውቶቡስ
- ሎት 2 ፡– የጋራጅ አገልግሎት ግዥ (የተሽከርካሪ የሰርቪስና የጥገና)
- ሎት 3፡– የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ (ለአዲስ አበባ)
- ሎት 4፡– የእንሰሳት መድኃኒት ግዥ
- ሎት 5፡– የድንኳንና የወንበር ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ስለዚህ በጨረታ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንዲትጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክሲ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁባቸውን ዕቃዎች መጫረቻ ሠነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የተጠየቀውን ወይም የሚወዳደሩበት ናሙና ማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በአዲስ አበባ፣ በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎቱ 100(አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋናው እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 9ኛ ፎቅ በሚገኘው በመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆኑን አለመሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን አለመሆኑን ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫት እንደካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 011-8-67-81-75
በአዲስ አበባ ከተማ የየካ
ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ጽ/ቤት