የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር የካ ክ/ከ/አ/ግ/ከ/
ቅ/ፅ/ቤት 001/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የሚከተሉትን እቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ – የደንብ ልብስ
- ሎት ሁለት – አላቂ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች
- ሎት ሶስት – ህትመትና የህትመት ውጤቶች
- ሎት አራት – የፅዳት እቃዎች
- ሎት አምስት –ቋሚ አላቂ የአይቲና የስቴሽነሪ እቃዎች
- ሎት ስድስት ቋሚ የአይቲና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት ሰባት –ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች
- ሎት ስምንት –የመኪና ዲኮር እቃዎች
- ሎት ዘጠኝ – የኮምፒዩተር ጥገና
- ሎት አሥር – የካዝና ጥገና ፣የፓርትሽን ስራ
- ሎት አሥራ አንድ– የመስተንግዶ ግዥ /ቆሎ/
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴከኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናልና ኮፒ” እና የፋይናንሻል የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናልና ኮፒ” የድርጅቱን ስም፣ አድራሻእና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት (ሎት) በመጻፍ በተናጠል በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 በግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለሎት አንድ፣ለሎት ሁለት፣ለሎት ሶስት ፣ ለሎት አራት፣ ለሎት አምስት ፣ለሎት ስድስት ፣ ለሎት ሰባት ፣ ለሎት ስምንት ፣ ሎት ዘጠኝ፣ ሎት አሥር እና ሎት አሥራ አንድ– ብር 3000 (ሦስት ሺህ ብር) ሊሆን፣ በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CP0 ከጨረታ ሰነዱጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ CP0 መስራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መገናኛ ለገሰ ፈለቀ ህንፃ ፊት ለፊት ወይንም ከመገናኛ ወደ 22 መስመር ወረድ ብሎ በሚገኘው አማረ አብረሃምና ቤተሰቡ ህንፃ ላይ በሚገኘው የካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተእ.ታ (ቫት) ጨምሮ ወይም ተእታ(ቫት) በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለፁ ከሆነ እታ (ቫት) ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላሲያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥና ፋይናንስ ቡድን ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ተጽ/ቤቱ እስከ 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡– 0116 68 41 08 /09 20 26 04 67/09 39 60 75 29 በመደወል ወይንም መገናኛ በሚገኘው ለገሰ ፈለቀ ህንፃ ፊት ለፊት ወይንም ከመገናኛ ወደ 22 መስመር ወረድ ብሎ በሚገኘው አማረ አብረሃምና ቤተሰቡ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች
ቢሮ የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት