ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የካ/አፀደ ህጻናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2013 ዓም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዢ መለያ ቁጥር 00/2013
- ሎት 1/የሰራተኛ የደንብ ልብስ
- ሎት 2 / ኣላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 3/ አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 4/ አላቂ የፅዳት እቃዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱትን እቃዎችን ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የዘመኑ ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር የሚያቀርብ
- የጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገብ ማስረጃ የሚያቀርብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ተጫራቾች የግዢ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 100.00/አንድ መቶ ብር በመከፈል በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድቦንድ/ ብር 3000.00/ ሶስት ሺ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው እስከ አስረኛው የስራ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 2፡30 ሰአት ጀምሮ ከተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት 10ኛቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ታሽጎ 9፡00 ሠዓት ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ እንዲሁም ከተጠየቀው እስፔሲፊኬሽን ውጪ እቃ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን እና የድርጅታቸው ማህተም አድራሻውን ማስፈር አለባቸው።
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ፦ በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን እስፓልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤምባሲ ጎን ባለው አስፓልት 100 ሜትር ገባ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116686087/0116674873 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡– ዋጋውን የሚሞላው በወሰዳችሁት የጨረታ ሰነድ ላይ ነው፡፡
የካ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት