ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/ 2013
በደ /ብ/ብ/ህ/ ከ/ መስተዳድር የካፋ ዞን የገ/ ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ለ2013 በጀት ዘመን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
* በዚሁ መሰረት
- የህክምና መሳሪያ እና መድሃኒት ግዥ
- የመኪና ጎማ ግዥ
- የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- የፅዳት እቃዎች ግዥ
- የደንብ ልብስ ግዥ
- የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች ግዥ
- የቧንቧ ዕቃዎች እና የህንፃ መገጣጠሚያ እቃ ግዥ
- የቢሮ ዕቃዎች ፈርንቸር ግዥ
- ህትመት አገልግሎት ግዥ
- ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አገልግሎትግዥ
ሲሆን ተወዳዳሪዎች የሚጠበቅባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የእቃ አቅራቢነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ሲችሉ
- ከተራ ቁጥር 3ኛ-6ኛ እና ለተራ ቁጥር 9ኛ ድረስ ለወጡ ጨረታዎች ናሙና በማቅረብ መጫረት የሚችል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ እሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ንብረት እ/ር ቢሮ ቁ22 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር ለእያንዳንዱ ጨረታ 100 አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር ሲፒኦ በባንክ የተመሰከረ ማቅረብ እና ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋጋ በመሙላት ቦንጋ ገ/ፃ/ሻዎ አ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ.22 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ላይ ፖስታዎችን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ16 ኛው ቀን ላይ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ቦንጋ ገ/ፃ /ሻዎ ኣሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ22 ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ ሙሉ በሙሉ እስከ ገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግምጃ ቤት /ንብረት ክፍል ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና እስከ በጀት ዘመን ማለቂያ ድረስ ተቋሙ ተጨማሪ ግዥ በመፈፀም ፍላጎት ሲያቀርብ ባሸነፈው ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ለማስያዝ በሆስፒታሉ ስም በዝግ አካውንት ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ እና ማሸነፉ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 5 አምስት ቀናት ቀርቦ የውል ስምምነት ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ
- ጨረታው የሚከፈተው ቦንጋ ገ/ፃ /ሻዎ አ/ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አ/ር ቢሮ ቁ22 ሲሆን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል ::
ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስቁ
0473310316/0473311798/ ያገኙናል፡፡
የገ/ፃድቅ ሻዎ አጠቃላይ
ሆስፒታል /ካፋ ቦንጋ