በድጋሚ የወጣ የግዢ የጨረታ ማስታወቂያ
የካቲት 23 ልዩ ፍላጎት የመ/ደ/ት/ቤት
- የደንብ ልብስ ፣
- የጽዳት እቃ፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- አላቂ የህክምና እቃዎች፣
- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣
- ቋሚ ዕቃዎች ፣
- ህትመትና የግድግዳ ላይ ትምህርታዊ ስዕሎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሳል ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚችሉት፡
በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 80 (ሰማኒያ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000(ሶስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ /cpo/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: እንዲሁም ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ሳምፕል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ማንኛውም ተጫራች የመሸጫ ዋጋውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አዘጋጅቶ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 8 መሳሚያ ወረዳ 6 ፖሊስ ጣቢያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
የየካቲት 23 ልዩ ፍላጎት የመ/ደ/ት/ቤት