ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 026/2012 ዓ.ም
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለሆስፒታሉ ግብአት አገልግሎት የሚውሉ
ሎት 1 የምግብና የላውንደሪ አውት ሶርስ
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ጽሑፍ ያለው፣
- የዘመኑን የመንግሥትን ግብር የከፈሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
- ለመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሪላንስ ማቅረብ አለባቸው።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም ፤ ጨረታው 10 የሥራ ቀናት ከ2፡30 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 ፐርሰንት የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቶች ቴክኒካል ሰነዶች እና የዋጋ ማቅረቢያዎች /ፋይናንሻል/ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽገው ለየብቻ መቅረብ አለባቸው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባውን ሰነድ ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጂናል እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒና ኦርጂናል በማድረግ በተለያዩ ፖስታዎች አሽጎ ለየብቻ እያንዳንዱን በማህተም በመምታትና የሚወዳደሩበትን ሎት በመጻፍ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግዢ ፈጻሚው የተሞላው ዋጋ ከነቫቱ እንደሆነ በመቁጠር ያወዳድራል::
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10 የሥራ ቀናት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ማንኛውም ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
- ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0946670707 በመደወል መጠየቅ ይችላል ::
አድራሻ 6 ኪሎ የካቲት 12 ሰማዕታት ሐውልት ፊት ለፊት
የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ