የት/ቤት ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለኩርፋ ጨሌ ወረዳ ልዩ ት/ቤት ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት/ለማሰራት ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች
- የሚፈለግበትን የመንግስት ግብርና ታክስ በህጉ መሠረት የከፈለና ፈቃዱን ያሳደሰ
- ታክስ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለውና የሚያቀርብ የ(ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የ(ቫት ተመዝጋቢነት መረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው።
- በመንግስት ግዥና ግንባታ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ
- በሚያቀርባቸው የግንባታ ዕቃዎችና የግንባታ ሥራ ጥራት የታወቀና ለዚህም ከታወቀ የመንግስት መስሪያ ቤት ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- የጨረታ ማስከበሪያ 1% (አንድ ፐርሰንት) በሲፒኦ ወይም የኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝርና የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን የግንባታ ዕቃ ሁሉ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ በራሳቸው አርማና ማህተም ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በትክክል በመጻፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በኩርፋ ጨሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ 27/2/2013 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ኣለባቸው።
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 2፣3 እና 4 ላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ሁለት ፎቶ ኮፒ በዋጋ ማቅረቢያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት አብረው ማሸግና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ27/02/2013 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡–ስርዝ ድልዝ ያለው የማይነበቡ የሚያደናግሩ ሰነድና ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0942240294 ፤0913787963 ይደውሉ።
አድራሻ፡–ምስ/ሐረርጌ ዞን ኩ/ጨሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
ሐ.ሶፊ ጠቅላላ ፕሮሞሽን ስራዎች