የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም
- ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸሮች/
- የደንብ ልብሶች የወንድና የሴት ጫማዎች
- ለፅዳት የሚውሉ ቁሳቁሶች
- የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ እቃዎች ወዘተ. በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ማሳሰቢያ፡– በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች
- የሚፈለግበትን የመንግሥት ግብርና ታክስ በህጉ መሰረት የከፈለና ፍቃዱን ያሳደሰ
- የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለውና የሚያቀርብ የ(VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የ(VAT) ተመዝጋቢነት መረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ያልታገደ
- በሚያቀርባቸው እቃ ጥራት የታወቀና ለዚህም ከታወቀ የመንግሥት መ/ቤት ማስረጃ የሚያቀርብ
- የጨረታ ማስከበሪያ 5000 /አምስት ሺህ/ የኢት. ብር ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር የያውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን እቃ በራሳቸው ወጪ እስከ ወረዳው ንብረት ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ የራሳቸው አርማና ማህተም ባለው ዋጋ ማቅረቢያ በትክክል በመፃፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ 27/12/2012 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1፣2፣3 እና 4 ላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ በዋጋ ማቅረቢያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት አብረው ማሸግና ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ27/12/12 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– ስርዝ ድልዝ ያለው የማይነበብ የሚያደናግሩ ሰነድና ማስረጃ ተቀባይነት የለውም
አድራሻችን፡– ምስ/ሐረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0942240294፣ 0913787963 ጠይቀው ይረዱ
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት