የከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል የሴቶች ማረፊያና ማረሚያ ቤት ማዕከል
የምግብ ጥራጥሬ ማጣፈጫ እና የማገዶ እንጨት እንዲሁም ለከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል
ለሲቪል ሠራተኞች የተለያዩ የሥራ ልብስና ጫማዎች
የጨረታ ማስታወቂያ
የከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል
- የጨረታ ቁጥር – 1 ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት የጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታ ቁጥር – 2 የሲቪል ሰራተኞች የሥራ ልብስና ጫማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ፤ በሥራው መስክ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በዕቃ ግዢ አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዲሁም ቲን ቁጥር (Tin Number) ተመዝጋቢ የሆነና ግብር ስለመክፈሉ የተሟላ ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ ጥራጥሬዎች እንዲሁም አትክልትና ማጣፈጫዎች የማገዶ እንጨት ለጨረታው የውል ማስከበሪያ ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሲቪል ሰራተኞች የስራ ልብስና ጫማዎች ለጨረታው የውል ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ (ፕሮፎርማቸው) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ቁጥር – 1 የምግብ ጥራጥሬ፤ ማጣፈጫዎችና የማገዶ እንጨት እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዢ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ቁጥር – 2 የሲቪል ሰራተኞች የስራ ልብስና ጫማዎች እስከ ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የግዢ ሥራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማረ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ለከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል ቃሊቲ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ግ/ቤታችን ማስረከብ አለባቸው:: ማረ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቃሊቲ በሚገኘው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000007971188 ቃሊቲ ማረ/ቤት እደ/ጥ/ማዕከል በሚል ገንዘቡን ገቢ ካደረጉ በኋላ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ሰነድ ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ፕሮፎርማቸው ላይ ዋጋ ሲፅፉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ጎላ ብሎ የሚነበብ ፅሑፍ መሆን ይገባዋል፡፡ በአሃዝና በፊደል መፃፍ ይጠበቅባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ቃሊቲ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡011-4 62-66-90 ወይም 011-4-39-25-39 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የከፍተኛ ጥበቃ ማረ/ቤት ማዕከል
የሴቶች ማረፊያና ማረሚያ ቤት ማዕከል